English | Español | 中文 | shqip | عربى | Français | Kreyòl Ayisyen| हिंदी | Tiếng Việt
ጥቅሞችንም ጨምሮ የ6 ወር ክፍያ ዋስትና አግኝተናል!
ማህበራችን መንግስት በድጎማ የሰጠውን ገንዘብ የአየር መንገዱ መስተንግዶ ሰራተኞች ለ6 ወራት ክፍያ እንዲያገኙና ጥቅሞቻቸው እንዲጠበቁ ሕግ ፅፏል!
አየር መንገዱ $50 ቢልዮን ድጎማ ያገኘ ሲሆን፤ ነገር ግን ግማሹ ለሰራተኞች ሲሆን $3 ቢልዮን የሚሆነው ደግሞ አየር መንገዱ ጋር ውል ላላቸው Skychefs፣ Gate Gourmet እንዲሁም ሌሎች የመስተንግዶ አቅራቢ ድርጅቶች ነው፡፡
6 ወር ጥቅም ሳይቀነስ ክፍያ ማግኘት 4 ወር ስራ ከማጣት ይሻላል!
መብትዎትን ይወቁ! ይህ ድል ለሰራተኞች ምን ማለት ነው፡
- የ Skychefs 90% ሰራተኞች ለ6 ወራት ክፍያና የጤና ጥቅሞቻቸውን ማግኘት ይቀጥላሉ፡፡
- ይህ በሌላ አባባል፡ Skychefs 90% ሰራተኞችን እስከ መስከረም 30 ለ6 ወራት መክፈል አለበት፡፡
- እስከ መስከረም 30 ድረስ Skychefs ለ6 ወራት 10 % ሰራተኞች በላይ መቀነስ አይችልም፡፡
- 6 ወር ጥቅም ሳይቀነስ ክፍያ ማግኘት 4 ወር ስራ ከማጣት ይሻላል!
በአዲሱ ህጋችን ሀይልና አብረን በጋራ በመቆም ከመስተንግዶ ድርጅቶች የሚከተሉት ነገሮች እንዲፈፀሙ እንጠይቃለን፡
- ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰራተኞች ስራ ሳይሰሩ ክፍያ እንዲከፈላቸው! አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰራተኞች ስራ እንዲሰሩና ነገር ግን ደህንነታቸው እንዲጠበቅ!
- 40 ሰዓት ክፍያና በስራ ዘመን ቆይታ መሰረት ያደረገ 0 የስራ ሰዓት መርሀግብ እንጠይቃለን፡፡
- ምንም ያህል ሰዓት ብንሰራም እንኳን 40 ሰዓት ክፍያ እንዲከፈለን እንጠይቃለን!
- ስራ እንዲሰሩ መርሀግብር የወጣላቸው ሰራተኞች ራሳቸውን ከቫይረሱ እንዲከላከሉ ደህንነቱ የተጠበቀ የስራ ሁኔታ እንዲኖራቸው እንጠይቃለን፡፡
- ስራው ደህንነቱ የተጠበቀ ካልሆነ Skychefs የስራ አጥነት ማመልከቻችንን ሳይነፍገን በፈቃደኝነት መቀነስ እንድንችል እንጠይቃለን፡፡
- ዕድሚያቸው ከ59 ዓመት በላይ የሆኑ ወይ የህክምና ማስረጃ ያላቸውንና በ COVID-19 ለመጠቃት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ የሆኑ ሰራተኞች ሀኪም እንዲሰሩ ካልፈቀደላቸው በስተቀር የስራ እረፍት ተስጥቷቸው የ40 ሰዓት ክፍያና ጥቅማጥቅሞች እንዲጠበቅላቸው እንጠይቃለን፡፡
- ለመስራት የሚገደዱ ሰራተኞች ተጨማሪ የአደጋ ግዜ ክፍያ እንዲከፈላቸው እንጠይቃለን፡፡