English | Español | 中文 | አማርኛ | shqip | عربى | Français | Kreyòl Ayisyen| हिंदी | Tiếng Việt
- እንደ LSG፣ Gate Gourmet እና የአየር መንገድ መስተንግዶ ለመሳሰሉ የአየር መንገድ ኮንትራት ድርጅቶች በ CARES ህግ አማካኝነት 3 ቢልዮን ዶላር ተመድቧል፡፡
- Sky Chefs (LSG) እንዲሁም Gate Gourmet (GG) ከሚያዝያ እስከ መስከረም 2019 እንደነበረው የፐይሮል ክፍያ እኩል መጠን እርዳታ (ብድር ያልሆነ) እንዲያገኝ አመልክቷል፡፡
- ከዛሬ ግንቦት 1 2020 ጀምሮ መንግስት ለ Sky Chefs ወይ Gate Gourmet ምንም ዓይነት ገንዘብ ለመስጠት አላፀደቀም ወይ አላከፋፈለም፡፡
- ሕጉ እንደሚያስቀምጠው ለድርጅቱ የሚሰጠው ማንኛውም ገንዘብ በቀጥታ ለፐይሮል ጥበቃ ድጋፍ ይውላል፡፡ ይህ ማለት፡
-
- የሰራተኞች ደሞዝና ጥቅሞች ክፍያ፡፡
- ያለፈቃድ መቀነስ አይቻልም፣ ለማንኛውም ሰራተኛ ከመንግስት ጋር ስምምነት ከፈረመ በኋላ እስከ መስከረም 30 ክፍያ ወይ ጥቅሞች አይቀነስም፡፡
- ሁሉም የሚከፋፈለው ገንዘብ የመንግስት ክትትልና ኦዲት ይደረግበታል፡፡
- ማህበራችን ለእያንዳንዱ ወጥቤት የሚከፈለው ማንኛውም ክፍያ ላይ ሙሉ ግልፀኝነት እንዲኖር ይጠይቃል፡፡ ልእኛ የሚገባንን ለማግኘት መታገል ይኖርብናል፡፡
- የአሜሪካ ኮንግረንስ አባላት ሌሎች CARES ሕግና ጠንካራና ተደራሽ የጤና እንክብካቤ ሽፋን፣ በእያንዳንዱ ወር ‹‹ማበረታቻ›› ክፍያ እንዲሁም የስራ አጥነት ጥቅሞች እንዲያፀድቁ እስክናደርግ ድረስ ይጠብቁን፡፡
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከኮሚቴው ወይ አዘጋጅ ጋር ይወያዩ